ሐምሌ 12፣ 2017 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የብርሃን አይነስዉራን አዳሪ ትምህርት ቤት ዳይሬክተሮች ፣መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች የመዝናኛ እና የአንድነት ፕሮግራም አካሄዱ።
መርሃ ግብሩ በቢሾፍቱ ከተማ ኖራ ሪዞርት የተካሄደ ሲሆን የቀድሞ የት/ቤቱ አመራሮች፣ የገላንና የመነን አዳሪ ትምህርት ቤቶች ዳይሬክተሮች እና ሌሎች የተጋበዙ እንግዶች ተገኝተዋል።
ፕሮግራሙን ያዘጋጀው የትምህርት ቤቱ ማህበራዊ ኮሚቴ ሲሆን የትምህርት ቤቱ የማህበራዊ ኮሚቴ ሰብሳቢ መምህር ከድር ረዲ መርሃ ግብሩ የተቋም ባህልን ለማጎልበትና ማህበራዊ ትስስርን ለማዳበር ያለው ሚና የጎላ መሆኑን ገልፀው ፕሮግራሙ እንደ ሃገራችን ባህል በምርቃት መርሃ ግብር እንዲጀመር የትምህርት ቤቱን አንጋፋ ሰራተኞችን ጋብዘዋል፡፡ አካዳሚክ ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ሆርዶፋ፤የስፖርት መምህር አቶ አስናቀ ሙለታና አቶ ወርቁ ጫኔ በአባታዊ ምርቃት ፕሮግራሙን አስጀምረዋል፡፡
በመቀጠልም የኬክ ቆረሳ መርሃ ግብር በቀድሞው የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተሮች በአሁኑ የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተሮችና በገላንና መነን አዳሪ ትምህርት ቤት ዳይሬክተሮች በጋራ በመሆን አከናውነዋል፡፡
በመጨረሻም የአብሮነት መርሃ ግብሩ እንዲሳካ አሰተዋጽዎ ላበረከቱት አካላት የእዉናና ምሰጋና ሰርተፍኬት ተበረክቶላቸዋል፡፡
የማህበራዊ ኮሚቴው ለፕሮግራሙ ታዳሚዎች በሙሉ መልካም የመዝናኛና አብሮነት ፕሮግራም እንዲሆን ተመኝቶላቸዋል፡፡
.