Berhan Blind Boarding Secondary School
Announcement Gamtaa Dubartootaa

Gamtaa Dubartootaa

09th June, 2025

የሴት ርዕሳነ መምህራን፣ የቡድን መሪዎች እና መመህራን የግንኙነት መርሃ ግብር  ተካሄደ።

(ግንቦት 20፣ 2017) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ብርሀን የአይነ ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት የ ሴት ርዕሳነ መምህራን፣ የሴት ቡድን መሪዎች እና  ሴት መመህራን የግንኙነት መርሃ ግብር   ተካሄደ።

የግንኙነት መርሃ ግብሩ  ዓላማ የተማሪዎች ችግሮችን እንዲፈቱ የሚረዱ ብቁ ባለሙያዎች እንዲሆኑ፣ ተባብሮ መሥራት እና መደጋገፍን ብዉስጡ የያዜ ሲሆን ዝግጅቱ እንደ ማሪያ ሞንቴሶሪ፣ ማላላ ዩሳፍዛይ እና ሳቪትሪባይ ፉሌ ያሉ ታዋቂ ሴት መምሀራንን በምሳሌት   በማንሳት  ተወያይተዋል።

እነዚህ በምሳሌንት የተጠቅሱ ሴቶች በፈጠራቸው፣ በጽናት፣በትምህርት እና በማህበራዊ እድገታቸው ላይ ባላቸው ተጽእኖ የተከበሩ ምሆናችዉን በዉይይታቸዉ አንስተዋል።ፕሮግራሙ  ርህራሄ፣ መግባባት እና የህይወት ትምህርትን የመሳሰሉ ቁልፍ  ባህሪያት ላይ አፅንዖት ሰጥቷል።

በመጨረሻም የት/ቤቱ ዋና ዳይረክተር ወይዘሮ ዉብአለም ደበበ ይህ ስብሰባ በሴቶች መካከል ለትምህርት አንድነት እና ሙያዊ እድገት ያለውን ኃይል አጉልቶ የሚያሳይንው ብለዋል፡፡

.

Copyright © All rights reserved.

Created with