የሰኞ ማለዳ የመምህራንና የአስተዳዳር ሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡
(ሰኔ 02/2017 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በብርሃን የዓይነ-ስውራን አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚዘጋጀው የመምህራንና ሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ የት/ቤቱ ዳይረክተሮች፣ መምህራንና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።
በርዕሰ ጉዳዩ ላይ እውቀታቸውን ያካፍሉት ከሙያ ትምህርት ክፍል መምህር የኔሰው አሰፋ ‘የኢትዮጲያ አረንጓዴ ልማት’ በሚል ረዕስ እዉቅታቸዉን አካፍሏል፡፡
በዚህ የእውቀት ሽግግር ፕሮግራም ኢትዮጵያ ከአለም አየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ አገራት መካከል አንዷ መሆኗን የአካባቢ ጥበቃ ድርጅት (UNEP) ጥናት እንደሚያሳየው ከገለጹ በኋላ በዚህ ረገድ የተሰሩ ስራዎችን በዝርዝር አስቀምጧል ።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በ2011 ዓ.ም የተጀመረው “የአረንጓዴ አሻራ” የችግኝ ተከላ እና አካባቢ ጥበቃ ዘመቻ በአራት ዓመታት ውስጥ 20 ቢሊዮን ችግኝ ተከል በማቅረብ የደን ሽፋንን ወደ 17 በመቶ እንዲያደግ መደረጉን ካቀረቡት ሰነድ መረዳት ተችሏል፡፡
ይህ ተግባራዊ መርሃ ግብር የአካባቢ ጥበቃን፣ የምግብ ዋስትናን፣ የውሃ ሃብትን፣ ብዝሃ ህይወትን እና ግሪን ሀውስ ለማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑንም አሰረድቷል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም የአረንጓዴ ልማት ቢሮ ተመስርቶ የከተማዋን ውበትና አካባቢ ጥበቃ በቀልጣፋና ውጤታማ መንገድ ለማሳደግ እየሠራ ሲሆን የመንግስት መስሪያ ቤቶችና ትምህርት ቤቶች ችግኝ ትከለዉ ላይ እንዲሳተፉና ብዙ ወጣቶችም የስራ እድል እንዲያገኙ መደረጉን በመረሐ-ግብሩ ማሰረዳት ችሏል።





.