Berhan Blind Boarding Secondary School
Announcement የስራ አፈጻጸም ግምገማ ከተማሪዎች ጋር ተካሂደ።

የስራ አፈጻጸም ግምገማ ከተማሪዎች ጋር ተካሂደ።

23rd June, 2025

የስራ አፈጻጸም ግምገማ ከተማሪዎች ጋር ተካሂደ።

 

(ሰኔ 15/2017 .) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ብርሃን የዓይነ-ስውራን አዳሪ /ቤት የስራ አፈጻጸም ግምገማ የተካሄደ ስሆን በግምገማዉ ላይ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳሉ የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተሮች፣መምህራንና ተማሪዎች ተገኝተዋል።

 

በግምገማው ወቅት  በትምህርት ቤቱ እስካሁን እየተሰሩ ላሉት ስራዎች እና ስነሱ ለነበሩት ጥያቄዎች ምላሽ እየተሰጣቸው መሆኑን አስተያየታቸውን የሰጡት ተማሪዎቹ በተሰሩት ስራዎችም ስደረጉ የነበሩት ድጋፎችን በማንሰት ለቀጣይም ይበልጥ ለመስራት ይጠቅማል ያሉትን ሀሰባችን አንስተዋል ።

 

ከተማሪዎቹ ለተነሱት አስተያየቶች እና ጥያቄዎች ማብራርያ የሰጡት አቶ ሲሳይ ለእነዚህ ጉዳዮች ማብራርያ ከመስጠቱ በፊት ማን ምን ማድረግ እንዳለበት ማወቅ ያስፈልጋል በማሌት ከትምህርት ቤቱ ጀምሮ በደረጃዉ ያሉት ባለድርሻ አካላት ለሚታዩት ለዉጦች እንደ ሰሩት ሁሉ አሁንም በጋራ መስራታ ያስፈለጋልነዉ ያሉት፡፡  

 

አቶ ሲሳይ አክለውም ትምህርት ቤቱ በበኩሉ የሚችለውን እየሰራ መሆኑንና በቀጣይም በተሻለ ሁኔታ በትኩረት እንደሚሰራ ገልፀው ቢሮው በቀጣይም እዚህ የተሰሩ ስራዎችን በመከታተልና በመገምገም ይሰራል ብለዋል።

 

የትምህርት ቤቱ ዋና ዳይረክተር ወይዘሮ ዉባለም ደበበ ወይዘሮ ውብአለም ዳባባ እየተሰሩ ያሉትን ስራዎች እና የተመዘገቡ ዉጤቶችን  ጠቅሰው  እንደ ትምህርት ቤት እየሰሩ መሆናቸውን እና ችግሮችን ለመፍታት ትምህርት ቢሮው ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ብለዋል።

 

በመጨረሻም በከተማዉ ባሉት በሶስቱ አዳሪ ትምህርት ቤቶች 12ኛ ክፍል ተማሪዎቸች መካከል ከ በተካሄደው የጥያቄና መልስ ውድድር ትምህርት ቤቱን ወክለው ለተወዳደሩና ላሸነፉት ተማሪዎች እውቅናና ሽልማት ተሰጥቷል።

.

Copyright © All rights reserved.

Created with